የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በሲያትል
YOU ARE INVITED!

YOU ARE INVITED!

ECA-LOGO-Final (2)

የኢትዮጵያዉያን ማህበር በብርትሽ ኮሎንብያ(ቫንኮቬር)

ETHIOPIAN COMMUNITY ASSOCIATION OF B.C

ለኢትዮጵያውያን ማኅበር በሲያትል

8323 Rainier Ave South Seattle, Washington 98118

August 5, 2015

ለተከበራችሁ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት፤

በቫንኩቨር የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ማኅበር ዓመታዊውን የበጋ ክብረ በዓሉን በ August 29, 2015 ያደርጋል። ይህ ዝግጅት ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈና በአካባቢያችን ዋና የመገናኛና ባህላችንን የማስተዋወቂያ መድረክ ነው፡፡ ስለዚህም ከእኛ ጋር በመሆን ይህንን ዓመታዊ ክብረ በዓል እንድታከብሩ በአክብሮት እንጋብዛለን።

በተጨማሪም በ September 12, 2015 ደማቅ የእንቁጣጣሽ ዝግጅት ይኖረናል። በተለያዩ ከተሞች ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ድምጻዊ ብርሃኑ ተዘራ በከተማችን ይገኛል። በዚሁም ቀን የእንቁጣጣሽን በዓል አብራችሁን በማክበር ለዝግጅታችን የበለጠ ድምቀት እንድትሰጡልን በአክብሮት እንጋብዛለን።

በተለይም በሲያትል እና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መልእክታችንን በማስተላለፍ እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር፤

Leave a Reply

Close Menu