The Ethiopian Community (ECS) Health Program works with Washington State to improve community well-being by providing health education that is culturally and linguistically appropriate. Accordingly, it shares various types of information by focusing on respiratory health, immunizations, preventive care, maternal and child health, mental health, and health services. This helps community members access accurate information to make informed decisions and protect their health.
የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ (ECS) የጤና ፕሮግራም፣ ባህልንና ቋንቋን መሰረት ያደረገ የጤና ትምህርት በመስጠት የማህበረሰቡን ደህንነት ለማሻሻል ከዋሽንግቶን ስቴት (Washington Sate) ጋር ይሰራል። በዚህም መሰረት በመተንፈሻ አካላት ጤና፣ በክትባቶች፣ በቅድመ መከላከል ህክምና፣ በእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ በአእምሮ ጤና እና የጤና አገልግሎቶችን ላይ ትኩረት በማድርግ የተለያዩ መረጃዎችን ያጋራል። ይህም የማህበረሰቡ አባላት ትክክለኛ መረጃ አግኝተው በቂ እውቀት ያለው ውሳኔ እንዲወስኑና ጤናቸዉን እንዲጠብቁ ይረዳል።
Respiratory Illnesses (የመተንፈሻ አካላት ሕመሞች)
Learn more about respiratory health, common respiratory illnesses, prevention strategies, and ways to protect yourself and your family. This section provides educational information and downloadable resources for community members.
ስለ መተንፈሻ አካላት ጤና፣ ስለተለመዱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች፣ ስለ መከላከያ ስልቶች እንዲሁም እራስዎን እና ቤተሰብዎን ስለሚጠብቁባቸው መንገዶች የበለጠ ይረዱ። ይህ ክፍል ለማህበረሰቡ አባላት የሚሆን የትምህርት መረጃዎችን እና የሚወርዱ (downloadable) መዝገቦችን ያካትታል።
What is Measles (ኩፍኝ ምንድን ነው)
Learn more about measles, its symptoms, how it spreads, prevention strategies, and the importance of vaccination. This section provides educational information and downloadable resources to help community members protect themselves, their families, and the broader community.
ስለ ኩፍኝ በሽታ ምንነት፣ ስለ ምልክቶቹ፣ እንዴት እንደሚተላለፍ፣ ራሳችንን እንዴት መከላከል እንደምንችል እና ስለ ክትባት ጥቅም ዝርዝር መረጃ እዚህ ያገኛሉ። ይህ ክፍል እርስዎ፣ ቤተሰብዎ እና አካባቢዎ ከበሽታው እንድትጠበቁ የሚረዱ የትምህርት መረጃዎችንና በቀላሉ ስልክዎ ላይ አውርደው የሚያነቧቸው መረጃዎችን ያካትታል።
Tuberculosis (TB) BASIC INFORMATION (የቲቢ መሰረታዊ መረጃ)
Learn more about tuberculosis (TB), its symptoms, transmission, prevention, testing, and treatment options. This section provides educational information and downloadable resources to help community members stay informed and protect their health.
ስለ ቲቢ በሽታ ምንነት፣ ስለ ምልክቶቹ፣ እንዴት እንደሚተላለፍ፣ ራሳችንን እንዴት መከላከል እንደምንችል፣ ስለ ምርመራውና ስለ ሕክምናው ዝርዝር መረጃ እዚህ ያገኛሉ። ይህ ክፍል እርስዎ እና አካባቢዎ ከበሽታው እንድትጠበቁና ራሳችሁን እንድታውቁ የሚረዱ የትምህርት መረጃዎችንና በቀላሉ ስልክዎ ላይ አውርደው የሚያነቧቸው መረጃዎችን ይዟል።
Basic of Immunization (የክትባት መሠረታዊ ነጥቦች)
Learn more about immunizations, recommended vaccines, and how vaccinations help prevent serious diseases and protect community health. This section provides educational information and downloadable resources for individuals and families of all ages.
ስለ ክትባቶች ጥቅም፣ ስለሚመከሩ የክትባት ዓይነቶች፣ እንዲሁም ክትባት ራሳችንን ከከባድ በሽታዎች ለመጠበቅና የማህበረሰባችንን ጤና ለመንከባከብ እንዴት እንደሚያግዝ ዝርዝር መረጃ እዚህ ያገኛሉ። ይህ ክፍል ለሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎችና ለሙሉ ቤተሰብ የሚሆኑ የትምህርት መረጃዎችንና በቀላሉ ስልክዎ ላይ አውርደው የሚያነቧቸው መረጃዎችን ይዟል።