
የንግድ መምሪያ (ኮሜርስ) በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ከሚገኙ 30 የታመኑ የማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር፣ ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ ለተገለሉ አነስተኛ ንግዶች በባህል እና በቋንቋ የታገዘ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል። የአነስተኛ ንግዶች ፍላጎት ሰፊና የተለያየ ነው። የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎቶችን እና ድጋፎችን ለማግኘት የሚገጥሙ እንቅፋቶችን ለማስወገድ የበለጠ መስራት አለባቸው። ምንም እንኳን ብዙ የንግድ ባለቤቶች የመንግስት እና የለጋሽ ድርጅቶችን የእርዳታ ፕሮግራሞች በቀላሉ እንዲያገኙ የሚረዷቸው ግንኙነቶች እና ግብዓቶች ቢኖሯቸውም፤ ትላልቅ እንቅፋቶች ግን ብዙዎቹ አናሳ ማህበረሰቦች ባለቤት የሆኑባቸውን እና ታሪካዊ በሆነ መልኩ አገልግሎት ያላገኙ አነስተኛ ንግዶችን እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን እነዚህን ፕሮግራሞች እንዳያገኙ ይከላከሏቸዋል።
የንግድ መምሪያው የአነስተኛ ንግድ የመቋቋም አቅም ግንባታ መረብን (ስሞል ቢዝነስ ሬዚሊየንሲ ኔትወርክ) ያቋቋመው፤ ከሁሉም ማህበረሰቦች የተውጣጡ የንግድ ባለቤቶች ስላሉት ጠቃሚ ሀብቶች እና ፕሮግራሞች መረጃ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው። የመረቡ የታመኑ የማህበረሰብ ድርጅቶች በባህል እና በቋንቋ ተስማሚ የሆነ የግንኙነት ስራ፣ የትርጉም አገልግሎት፣ ድጋፍ እና ትምህርት በመስጠት፤ የንግድ ባለቤቶች የሚፈልጉትን መረጃ ከሚያምኗቸው ሰዎች እንዲያገኙ ያደርጋሉ።
በሲያትል የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ (Ethiopian Community in Seattle – ECS) በዚህ ግዛት አቀፍ መረብ ውስጥ ካሉ የታመኑ የማህበረሰብ አጋሮች አንዱ ነው። እኛም በተለይ በስደተኞች እና በባዕድ ሀገር ተወላጆች ባለቤትነት ለተያዙ አነስተኛ ንግዶች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች በባህል እና በቋንቋ ተስማሚ የሆነ የግንኙነት ስራ፣ የአንድ-ለአንድ የቴክኒክ ድጋፍ እና የመረጃ አሰጣጥ አገልግሎት እንሰጣለን። በታመነ ግንኙነት፣ በቋንቋ ተደራሽነት እና ቀጥተኛ መመሪያ በመስጠት፤ ECS የንግድ ባለቤቶች ያሉትን ፕሮግራሞች እንዲረዱ፣ ማመልከቻዎችን እንዲያሟሉ እና እድገታቸውን እና የረጅም ጊዜ ጥንካሬያቸውን ለሚያረጋግጡ ግብዓቶች እንዲገናኙ ይረዳቸዋል። ይህንን እድል ለሰጠን ለስሞል ቢዝነስ ሬዚሊየንሲ ኔትወርክ ቡድን ምስጋናችንን እናቀርባለን።
እርዳታ ለማግኘት ከዚህ በታች ባሉት ስልኮችና ኢሜሎች ያግኙን፡፡ እናመሰግናለን!
ስልክ፡ ተስፋዬ 1(206)5353079 ወይም አብርሃም 1(206)4822429
ኢሜል፡ tesfayef@ecseattle.org or abrahama@ecseattle.org
Commerce is partnering with 30 trusted community organizations across Washington State to provide culturally and linguistically relevant assistance to
historically underserved small businesses. The needs of small business are vast and varied. State agencies must do more to break down barriers to services and
support. While many business owners have connections and resources that help them tap into government and philanthropic aid programs, enormous barriers prevent many minority-owned and historically underserved businesses and nonprofits from accessing those same programs.
Commerce established the Small Business Resiliency Network to ensure business owners from all communities could be informed about important resources and programs available to them. The network’s trusted community organizations provide culturally- and linguistically-appropriate outreach, translation,
assistance and education to ensure business owners can find the information they need from people they trust.
Ethiopian Community in Seattle is one of the trusted community partners in this statewide network. We provide culturally and linguistically appropriate outreach, one-on-one technical assistance, and navigation support to small businesses and nonprofits, particularly those owned by immigrants and refugees. Through trusted relationships, language access, and hands-on guidance, ECS helps business owners understand available programs, complete applications, and connect to resources that strengthen their stability, growth, and long-term resilience. We are thankful to the SBRN group for providing us with this opportunity. For support, please call or email using the information below. Thank you.
Phone: Tesfaye 1(206)5353079 or Abraham 1(206)4822429
Email: tesfayef@ecseattle.org or abrahama@ecseattle.org
RESOURCES
የምግብ ቤት፣ የአዋቂዎች ቤተሰብ መርጃ መኖሪያ (Adult Family Home) እና የፍራንቻይዝ ንግድ እንዴት እንደሚከፈት የሚገልጹ በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መረጃዎችን ከታች ይገኛሉ። ይህ ስራ የተሰራው ከስሞል ቢዝነስ ሬዚሊይንሲ ኔትወርክ በተገኘ ድጎማ ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡
ሁሉም መረጃዎቹ በአራቱም ቋንቋዎች ስለሚገኙ፣ ሰነዱን ለመክፈት ወይም ለማውረድ ከታች በሚመርጡትን ቋንቋ ላይ ይጫኑ።
Thanks to the funding from SBRN, here are some resources in English, Amharic, Oromigna and Tigrigna on how to open a restaurant, adult family home and franchise business.
Resources are available in multiple languages. Click on your preferred language below to open or download the document.